Log in

Welcome To Austin Area Mutual Aid (EDIR)

       የኦስተንና አካባቢው መረዳጃ እድር

እንኳን ወደ ድህረ ገጻችን በደህና መጡ!!!






For EDIR Members or new applicants - Please contact Austin Mutual Aid EDIR phone number 512-717--1534 by calling or through text if you need urgent assistance and for any information or inquiry you may need. Thanks!


ዜና እረፍት/ ማስታወቂያ


ወይዘሮ እማዋይሽ አለሙ እኝህ ነበሩ

April 05, 1969 - May 3, 2022

የኦስተንና አካባቢው መረዳጃ እድር ሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ የእድራችን አባል የነበሩት የእህታችን የወይዘሮ እማዋይሽ ገሰሰ አለሙን ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ስንገልጽ ጥልቅ ሐዘን እየተሰማን ነው። ወይዘሮ እማዋየሽ ባደረባቸውን ህመም በህክምና ለረጅም ጊዜ ሲከታትሉ ቆየ ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በቤተሰብና ዘመድ አዝመድ ተከበው በጸበልና በጸሎት ክትትል ሲያደርጉ ቆይተው May 3, 2022 ከዚህ ዓለም የተለዩ ሲሆን የቀብር ሥነስርዓቱም ወዳጅ ዘመድ በተገበት በአዲስ አበባ ከተማ ተፈጽሟል:: ወይዘሮ እማዋየሽ የሁለት ልጆች ማለትም የሃይማኖትና የአቤል እሸቱ እናት ነበሩ፡፡

ይህንን አሳዛኝ ክስተት ለአባሎቻችን በወቅቱ ሳናሳውቅ በመዘግይታችን ይቅርታ እየጠይቅን ይህም ሊሆን የቻለው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች እንደሆነ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ በመጀመርያ የወይዘሮ እማዋይሽ ተወካይ ከእድሩ ጋር ግንኙነት ሳያደርጉ ለረዥም ጊዜ በመቆየታቸው የመዘግየት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሁለተኛ ለእድሩ ቆይቶ የቀረበው የሞት ምስከር ወረቀት ደግሞ ከእድሩ የአሰራር ልምድ ጋር ትንሽ ልዩነት ስለነበረው ያንን ልዩነት ለማስተካከልና ለማጣጣም ተጨማሪ ጊዜ መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ ተግኝቷል፡፡

ሁላችሁም እንደምታውቁት እድራችን በሕገ ደንባችን መሰረት ሁሉም ተፈላጊ ማስረጃዎች ተሟልተው እስኪገኙና ለሟች ቤተሰብ የእድሩን እርዳታ ሳይከፍል አባላቶቹን መዋጮ ስለማይጠይቅ የመዋጮ ክፈሉ ማሳሰቢያ ማስታወቂያ ለማውጣት እስካሁን አልተሳካም ነበር፡ ሆኖም ግን አሁን ሁኔታዎች ተሰተካክለው የእድሩ እርዳታ ወይዘሮ እማዋይሽ ተወካይ ሙሉ ክፍያው በቅርብ ስለተፈጽመ ወጪውን መልሶ ለመተካት የሚደርስባችሁን $25 በግለስብ አባል መዋጮ በአስቸኳይ እንድታዋጡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የኦስተንና አካባቢው መረዳጃ እድር ሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ

April 15, 2024

In Loving Memory of

Woizero Emawayish Alemu

April 05, 1969 - May 3, 2022

With heavy hearts, we announce the passing of our esteemed sister, Mrs. Emawaysh Gesesse Alemu, a valued member of the Austen Area Mutual Aid (EDIR). Mrs Emawaysh had been bravely battling illness for an extended period. As her health declined, she returned to Ethiopia, where she peacefully passed away on May 3rd, 2022 surrounded by her loved ones. Her funeral services were held in Addid Ababa, Ethiopia.

We would like to apologize for the delayed notification of this sad event to our EDIR members, which occurred due to two main reasons. Firstly, there was a prolonged absence of communication from the designated representative to the EDIR. They didn’t reach out to the Executive Committee immdiately to submit the necessary documentation and start the process of providing the required EDIR benefits. Secondly, upon receiving the request, the death certificate submitted did not align with EDIR documentation requirements and standard practice, requiring additional time to resolve the issue.

 Once resolved, the full amount of EDIR benefit was promptly paid recently to the designated representative of the family, per the requirements of the EDIR By-laws. Traditionally, our EDIR practice refrains us from soliciting replenishment contributions from members until the full EDIR benefits is paid to the designated representative of the family. With the completion of EDIR payments, we now kindly request that each member contribute $25 to replenish the total amount paid, as outlined in the EDIR by-laws,.

The Executive Committee

Austen Area Mutual Aid (EDIR)

April 15, 2024





=================================================================================



==============================================================================



=========================================================================


=======================================================================


========================================================================

=========================================================================

ዜና እረፍት 


በመሆኑም ይህ እድር ከማንኛውም የሃይማኖት ተቋምና ፖለቲካ ቡድን ገለልተኛ እንዲሁም ከዘር፣ከብሄር፣ከክልል ወይም ከጐሳ ልዩነት አመለካከት ነፃ ነው።

The association is not affiliated with any religious or political organizations and does not advocate on behalf of any race, place of origin or ethnicity.

News ዜና እረፍት

  • No news for today

Austin Area Mutual Aid (EDIR)

የዚህ እድር አስፈላጊነትና ሙሉ ትኩረት በአባል ወይም በአባል ቤተሰብ ላይ በሞት ምክንያት ሐዘን ሲደርስ የችግሩ ተካፋይ በመሆን በተለይም ለቀብር ስነ-ሥርዓት ማስፈጸሚያ ወይም አስከሬን መላኪያ ለሚያስፈልገው ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ ጫናን በመቀነሰ ረገድ ለመረዳዳትና ለመተጋገዝዝ ነው።

The purpose of the association is for members to help comfort and assist each other in the event of death of a member or the family of a member of the association by providing comfort and assisting in the cost of funeral services or transportation of the deceased.


The association will serve its members as a mutual assistance association traditionally known as “EDIR” in Ethiopian communities.  The association is registered as a non-profit organization in the state of Texas.

ይህ ማህበር በኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ዘንድ ባህላዊ  ተለምዶ አጠራር  እድር  ተብሎ የሚታወቀው ሲሆን የራሱን አባላትየሚያገለግል የመረዳጃ ማህበር ነው:: 

እድሩ አትራፊ ያልሆነ ድርጅት ሆኖ በቴክሳስ ስቴት ውስጥ በህጋዊ  ደረጃ የተቋቋመ ነው::


አባል ይሁኑ

Click Here To  Register

ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

Click Here To  Download Registration Form  የመመዝገቢያ ቅጽ ይህንን በመጫን ያግኙ

Please Click here to go to Austin Edir Paypal


Austin Edir Hosted The First Community Picnic

Recent forum updates

  • There are no forum topics to display.

New Memebers

Powered by Wild Apricot Membership Software